"hailu" poems
Mom is such
A special word
The loveliest
I've ever heard.
A toast to you
Above all the rest
Mom, you're
So special
You are simply
the best!
እማ
‹እማ› ልዩ ቃል ነው
በጣም ተወዳጅ
ሠምቼ ከማውቀው!
ብርጭቆአችንን እናንሳልሽ፣
ከሁሉም በላይ ከፍብለሽ፣
‹እማ› አንቺኮ ልዩ ነሽ
በቃ በትንሹ አቻም የለሽ!
(በሔለን ስቲነር ራይስ)
Mar 21, 2016
Mar 21, 2016 at 10:05 AM UTC
My baby, my burden,
Tomorrow the morn
I shall go lighter
And you will be born.
I shall go lighter
And heavier too
For seeing the burden
That falls up on you
The burden of love
The burden of pain
I'll see you bear both
Among men once again.
Tomorrow you'll bear it
Your burden alone,
Tonight you have no burden
That is not my own.
My baby my burden
Tomorrow the morn
I shall go lighter
And you will be born.//
የሜሪ ሸክም
ልጄ የኔ ሸክም የኔዳ
ነገ በማለዳ
እፎይ እላለሁ
አንተን እገላገላለሁ፣
ግና አንተን ብገላገልም
ሸክሜ አይቀልም
ምክኒያቱም ሳስበው
ያንን ሁሉ ጭንቅ
አንተን የሚጠብቅ
እላለሁኝ ሥቅቅ!
የፍቅርን ሸክም
የስቃይን ሸክም
በፅናት ሁለቱንም
አያለሁ ከሰውልጆች ጎራ
ዳግም ስትጋራ!
ነገ ብቻህን
ትጋፈታጣለህ ሸክምህን
ግና ማምሻውን
የኔ የማይሆን ምንም
ሸክም የለህም!
(ኢሌኖር ፍራጂዮን)
Dec 29, 2015
Dec 29, 2015 at 2:54 AM UTC
(Storms Bring Out the Eagles But The Little Birds
Take Cover )
When the “storms of life” gather darkly ahead,
I think of these wonderful words I once read
And I say to myself as “threatening clouds” hover
Don’t “fold up your wings” and “run for cover”
But like the eagle “spread wide your wings”
and “soar far above” the trouble life brings,
For the eagle knows that the higher he flies
The more tranquil and brighter become the skies...
And there is nothing in life God ever asks us to
bear
That we can’t soar above “On The Wings Of A
Prayer,”
And in looking back over the “storm you passed
through”
You’ll find you gained strength and new courage,
too,
For in facing “life’s storms” with an eagles wings
You can fly far above earth’s small, petty things.
ወጀብ ንስሮችን ያወጣል
(ግና ትናንሽ ወፎች ከመጠለያ ይመሰጋሉ)
የሕይወት ወጀብ ሲሰባሰብ፣
ደሞም ከስሎ ከላዬ ሲሳብ፣
እገባለሁ ማሰብ፣
ግሩም ምክሮችን እነኚህን፣
በአንድ ወቅት የሰማሁትን!
‘ለራሴ እንደዚህ እላለሁ
አስፈሪ ደመናዎች ሲያንዣብቡ፣
ክንፋችሁን አታስገቡ፣
ደሞም ሮጣችሁ
ሆናችሁ ጉጉ፣
ከመጠለያ አትመሰጉ!
ግን እንደንስር ክንፋችሁን ዘርጉ፣
ሕይወት ከሸከፈው ችግር በእቅፉ፣
ሽቅብ ሰንጥቃችሁ ተንሳፈፉ!
ምክንያቱ ያውቃል ንስር፣
ሽቅብ ሰንጥቆ ሲበር፣
ሰማዩ እንደሚቀየር፣
ወደብሩህ ጠፈር፣
ሰላምና መረጋጋት፣
ያደረጉት ግዛት!’
ሕይወትን ካጤንነው፣
እንድንቋቋመው የተጠበቅነው፣
ነገር ወይ ክስተት፣ ዘበት፣
በፀሎት ክንፍ፣ የማንለው እልፍ!
ያን በወጀብ የተናጥንበት
የትናንት ሕይወት፣
በምልሰት ስንመለከት፣
እናስተውላለን
አዲስ ተስፋና ብርታት፣
እንደሚሆኑን ተደራቢ ሀብት!
ሽቅብ በንስር ክንፍ፣
የሕይወትን አውሎንፋስ
ጥሳችሁ ስትሉ እልፍ፣
የመሬትን ጥቃቅን አለመመቻቸቶች
ረግጣችሁ፣ ትንሳፈፋላችሁ!
(በሔለን ስቲነር ራይስ)
Apr 7, 2016
Apr 7, 2016 at 8:12 AM UTC
O child of war, preserve your weapon,
For future children let it stay,
For they will come and ask their question
What was the world like in our day?
For them, born under stars more lucky,
It will be hard to understand
How could the sky have been exploded
While battles raged on see and land?
How,flowing black with blood,could rivers
Rock,bridges bombs had battered down
They'll never see it-as you never
Saw sunshine in the world around.
Preserve your weapon,little eagles,
Of many battle it will tell
Of days ferocious and heroic
For grandson to remember well.
ሰባዊ ቀንበጥ አርበኞች
ምስኪን ልጆች
ሰባዊ ቀንበጥ አርበኞች
መሳሪያችሁን በደንብ በቅርስነት አስቀምጡ
ለአምሳያዎቻችሁ በዘመን ሃዲድ ለሚመጡ
ምክንያቱም በኛ ጊዜ
ሉላዊ ገጽታው እንዴት እንደነበረ
መጠየቃቸው ስለማይቀር!
ምክኒያቱም እድለኛ ሆነው ለተወለዱት
ለማስረዳት ስለሚያዳግት እንዴት
ሰማዩ እንደተናጠ በፍንዳታ
በመሬት በባህር ጦርነት
ሲካሄድ ያላፍታ-ማለት ልክ
እናንተ የሰላም ጸሃይ የምትስተዋልበት
ሰማይ እንዳላያችሁት!
ጠይም የደም ጎርፍ እንዴት አድርጎ
የቦንብ ድልድይ ፍርስራሽ
እንደወሰድ ጠራርጎ !
ለልጅ ልጅ ስለሚዘከር ስለበርካታ
የጅግንነት የአይበገሬነት ውሎ
አደራ መሳሪያች ሁን በደንብ አኑሩ ልጆች
ተናንሽ ንስሮች !
በ ሳሎ ሜዳ ነሪስ
ትርጉም አለም ሃይሉ
(ሉትኒያ በናዚ በተወረረችበት ወቅት ገጣሚዋ በግጥም ወታደሮችን ታበረታታ ነበር። አንድ ህጻን ወታደር የስዋን ግጥም ከጋዜጣ ቀዶ የደረት ኪሱ ይዞ በማሺን ጋን ተመቶ እንደሞተ ተገኝትዋል)
Apr 11, 2016
Apr 11, 2016 at 10:54 AM UTC
I bent again unto the ground
And I heard the quiet sound
Which the grasses make when they
Come up laughing from the clay
--We are the voice of God!—they said
Thereupon I bent my head
Down again I might see
If they truly spoke to me.
But, around me, everywhere,
Grass and tree and mountain where
Thundering in mighty glee,
--We are the voice of deity!—
And I leapt from where I lay:
I danced upon the laughing clay፡
And, to the rock that sang beside,
--We are the voice of God!—I cried.
የእግዚአብሔር ድምፅ
ዳግም ወደ ምድር እንዳጎነበስኩ
ጥርት ያለ ድምፅ አደመጥኩ
ቄጤማዎች የሚስደምጡት ፈንድቀው
ብቅ እዳሉ ሸክላ አፈሩን ሰንጥቀው
“የእግዚአብሔር ድምፅ ነን አድምጡን!”
እዛው ጭንቅላቴን ዝቅ አድርጌ
ዓይኔን ሰደድኩ ወደ ግርጌ
በርግጥ እኔን አያናገሩ እንደው
ማወቅ ፈልጌ፣
ግን በዙሪያዬ በየስፍራወ
ሳሩ ዛፉና ተራራው
በደስታ እንደ መብረቅ
ነበር የሚያስተጋባው
‹‹የአምላክ ድምፅ ነን
አድምጡን!››
ጋድም ካልኩበት
በሐሴት የሚፍለቀለቅ መሬት
ዘልዬ በፍጥነት
ቀጥ ብዬ ቆምኩ
እንደዛ እዳደረግኩ
በተመስጦ እያሸበሸብኩ
ከጎኔ ለሚዘምረው ኮረብታ
እኔም በደስታ
‹‹የእግዚብሔር ድምፅ ነን!›› አልኩታ፡፡
(ጄምስ ስቲፈንስ)
Dec 30, 2015
Dec 30, 2015 at 9:09 AM UTC
Lion beating the drum
wind kisses green leaves
shining sun smiles
Sep 6, 2016
Sep 6, 2016 at 8:41 AM UTC
Here’s is an example from
A butterfly;
That on a rough, hard rock
Happy can lie,
Friendless and all alone
On this unsweetened stone.
Now let my bed be hard,
No care take I;
I will make my joy
Like this
Small butterfly,
Whose happy heart has power
To make a stone a flower.
ምሳሌ
አነሆ ምሳሌ ለኛ
ከቢራቢሮ
አልቦ ጓደኛ
ሆና ብቸኛ
የድንጋይ አልጋው
ባይሆንም ደንበኛ
ሻካራ ደረቅ አለት ላይ
ረክታ የምትተኛ፣
እኔም አልጋዬ ቢሆን ደረቅ
ከቶ አልሰቀቅ
ግድ የለም አልቸገር
አሁን ደስታዬን ከዚች
ቢራቢሮ ልበደር፣
ልቧ ጉልበት ያለው
አለቱን ወደአበባ ለመቀየር!
(በዊሊያም ሔነሪ ዳቪስ) //
Dec 31, 2015
Dec 31, 2015 at 8:36 AM UTC
Some say the world will end in fire
Some say in ice
From What I tasted of desire
I hold with those who favour fire.
But if I had to perish twice,
I think I knew enough of hate
To know that for destruction ice
Is also great
And would suffice.
እሳትና በረዶ
‹‹ይህች ዓለም
በሳት ትጠፋለች!››
ይላሉ አንዳንዶች
‹‹በበረዶ!›› ሌሎች፡፡
ፍላጎቴን በምኞት ሚዛን
እንደፈተሽኩት
እሳት ከሚሉት ጎራ ነው ያለሁት!
መጥፋት ካለብኝ ግን ዳግም
ለውድመት በረዶም
እንዳለው ትልቅ ጉልበት፣
እንዲሁም ተመጣጣኝነት፣
ከምሬት ፣በስፋት፣
አግኝቼአለሁ ትምህርት!
(ሮበርት ፍሮስት) //
Jan 25, 2016
Jan 25, 2016 at 9:27 AM UTC
I was angry with my friend,
I told my wrath, my wrath did end.
I was angry with my foe;
I told it not, my wrath did grow.
And I watered it with fears,
Night and morning with my tears;
And I sunned it with smiles,
And with soft deceitful wiles.
And it grew both day and night,
Till it bore an apple bright
And my foe beheld its shine
And he knew it was mine.
And into my garden he stole
When the night had veiled the pole,
In the morning glad I see
My foe outstretched beneath the tree.
()
መርዛማው ዛፍ
በጓደኛዬ ተናድጄ ነበር
ምሬቴን እንደተነፈስኩ፣
ከብስጭት ተገላገልኩ!
በባላንጣዬ ተናድጄ ነበር
ምሬቴን ስለአፈንኩት አፀደቅኩት፣
የፍርሐትን እንባ ያለፋታ
አጠጣሁት ቀንና ማታ
ፍሬ አፈራ ማራኪ ለእይታ!
ጠላቴ የኔ መሖንዋን እያወቀ
በፍሬዋ ተሰረቀ፣
እናም ጨለማን ተገን አርጎ
ገባ ከአትክልት ቦታዬ ሰርጎ፡፡
ጠዋት ተመለከትኩ
በደስታ በአንክሮ፣
ጠላቴ ዛፏ ስር ተዘርሮ!
Jan 11, 2016
Jan 11, 2016 at 10:17 AM UTC
What do I owe to you
Who loved me deep and long?
You never gave my spirit wings
Nor gave my heart a song.
But oh, to him I loved,
Who loved me not at all,
I owe the open gate
That leads through heaven’s wall!
(By Sara Teasdale)
እዳ
በደንብ ጠበቅ አድርገህ ላፈቀርከኝ
የምከፍለው ምን ወሮታ አለኝ?
ለነፍሴ ክንፍ አለገስካት
ለልቤም መዝሙር አልሰጠሃት፣
ግን፣ ውይ፣ ለወደድኩት ላላፈቀረኝ፣
ዕዳ አለብኝ፣ በሩን ያለው ከፈት፣
በግድግዳወ አርጎ ሠተት
የሚያዘልቅ ወደ ገነት!
(ሳራ ቲሰዳል) /
Mar 17, 2016
Mar 17, 2016 at 5:10 AM UTC
She stood breast high amid the corn
Clasp’d by the golden light of morn,
Like the sweetheart of the sun,
Who many a glowing kiss had won.
On her cheek an autumn flush,
Deeply ripen’d;—such a blush
In the midst of brown was born,
Like red poppies grown with corn.
Round her eyes her tresses fell,
Which were blackest none could tell,
But long lashes veil’d a light,
That had else been all too bright.
And her hat, with shady brim,
Made her tressy forehead dim;—
Thus she stood amid the stooks,
Praising God with sweetest looks:—
Sure, I said, Heav’n did not mean,
Where I reap thou shouldst but glean,
Lay thy sheaf adown and come,
Share my harvest and my home.
ሩት
እስከ ጡቷ ከፍታ
የተንጣለለ የበቆሎ ማሳ ውስጥ ገብታ፣
የማለዳው ወርቃማ ጮራ
በዙሪያዋ ዘሃውን እያደራ፣
ሠምጣ ቆመች፣ በእጹብ ድንቅ ግርማ
እንደፀሐዩ ፍቅረኛ ደጋግማ
በጨረር ተስማ ተሸላልማ፡፡
ልክ ከበቆሎ የማሳ ዳራ
ብቅእዳለቸ ዓይን የምታስር አበባ
የተገኘች ከጠይሞች ጎራ፣
እንደበሠለ ፍሬ እንደጎምራ
ጉንጮችዋ ቀልተዋል አፍራ!
ብርቅዬ ጥቁር ሐር
የፀጉሯ ዛላ ተዘናፍሎ
ይስተዋላል ቅንጦቿዋን
ደገፍ ደገፍ ብሎ፣
ግና የዓይኖቿ ሽፋሽፍት
ብርሃን እምቅ አድርገዋል ድብቅ
አሊያ በጣም የሚያንፀባርቅ!
የኮፍያዋ ጥላ ፊቷን አጠይሞት
ከበቆሎው ምርት ቆማለች
ሐአሴት እያደረገች፣
አምላኳን እያመሰገነች!
በርግጥም አልኩ
አምላክ አላሰበም
እኔ ሳጭድ እሷ እንድትሸከም፡፡
በክርንሽ የሸከፍሽውን ለቀሽ
ወደኔ ነይ፣
ምርቴና ቤቴን ተካፈይ!
(ቶማሰ ሁድ) //
Feb 2, 2016
Feb 2, 2016 at 8:05 AM UTC
God gave you your daughter
For such a little while;
He put a bit of heaven
In the sunshine of her smile.
He took dust from
The brightest twinkling stars
And made her sparkling eyes;
And now, she’s gone back home to God,
To play up in the skies.
And though she left so quickly
That your hearts are grieved and sad,
We know she lives with God
And her small heart is glad.
And though your precious darling
Was just a rosebud small;
She’ll bloom in all her beauty
On the other side of the wall.
ለጥቂት ጊዜ
እግዚአብሔር አላችሁ
“ሚጡን ለጊዜው እንካችሁ!”
አቤት ከንፈርዋ ሲፈለቀቅ፣
የፀሐይ ጮራ ሲለቅ፣
ናሙና የገነት፣ የታተመበት!
ደሞም ሰራ፣
ዘግኖ አቧራ፣
ከብሩህ ከዋክብት፣
ዓይኖች የሚረጩ
የቀለም እርችት!
ግልፅ ነው እንደምትኖር፣
ከእግዚአብሔር ጋር፣
ደሞም እናውቅ፣
ትንሻ ልቧ
በሐሴት እንደምትጥለቀለቅ!
ምንም እንኳ ውድ ልጃችሁ
ብትሆንም ለጋ እንቡጥ ፅጌረዳ፣
እርግጥ ነው በስቲያ ከዛኛው ግርግዳ፣
ደምቃ እንደምትፈነዳ!
(በሔለን ስቲነር ራይስ)
May 6, 2016
May 6, 2016 at 8:57 AM UTC
Life is a mixture of sunshine and rain,
Laughter and pleasure, tear-drops and pain;
All days can’t be bright, but it’s certainly true,
There was never a cloud the sun didn’t shine
through.
So just keep on smiling whatever betide you,
Secure in the knowledge God is always beside
you.
And you’ll find when you smile your day will be
brighter
and all your burdens will seem so much lighter.
For each time you smile you will find it is true
SOMEBODY, SOMEWHERE will smile back at
YOU!
And nothing on earth Can make life more worth-
while
than the sunshine and warmth of a BEAUTIFUL
SMILE
በፈገግታ ውስጥ የፀሃይ ብርሃን አለ
ሕይወት ናት ድብልቅ፣
የመሰቀቅ፣ የመሆን ፍልቅልቅ፣
ደሞም ዝንቅ፣
የውሽንፍር የፀሐይ ጮራ፣
የእንባ አዝመራና የመከራ!
ብሩሕ ቀን ዘወትር እንጠብቅ፣
ግን የለም
ፀሐይ፣ ደመና ሰንጥቃ
ያላለችበት ብቅ!
ሕይወት ብትወጠር ብትታጨቅ፣
በሁኔታዎች ያሸረቡ ልብ እንዲወድቅ፣
ገጽታችን ይብራ በፈገግታ ይድመቅ፣
ሸክፈን የእምነት ስንቅ፣
እግዚአብሔር ብዙ ከኛ እንደማይርቅ!
ስትስቁ ቀኑ ብሩሕ እንደሚሆን ታያላችሁ፣
ደሞም እንደሚቀል ጭነታችሁ!
ለፈገግታ ስትሰጡ ቦታ፣
ታዳብራላችሁ ለእይታ፣
የሆነ ሰው ከሆነ ቦታ፣
እንደሚከፍል ውለታ፣ የፈገግታ!
እንደማራኪ ፈገግታ የሚጥም፣
የሕይወት ቅመም፣
በመሬት ላይ ምንም!
(በሔለን ስቲነር ራይስ)
Mar 30, 2016
Mar 30, 2016 at 8:39 AM UTC
Out of the night that covers me,
Black as the pit from pole to pole,
I thank whatever gods may be
For my unconquerable soul.
In the fell clutch of circumstance
I have not winced nor cried aloud.
Under the bludgeoning of chance
My head is ****** but unbowed.
Beyond this place of wrath and tears
Looms but the Horror of the shade,
And yet the menace of the years
Finds and shall find me unafraid.
It matters not how strait the gate,
How charged with punishments the scroll,
I am the master of my fate,
I am the captain of my soul.
በጨለማ ውስጥ
ከጥግጥግ ከከበበኝ
ድቅድቅ ጨለማ
ለማይበገረው መንፈሴ
ለአምላክ ያለህ የምስጋና ዜማ
ነኝ የማሰማ፣
ሑኔታዎች ቢያሸርቡም
ተሰቅቄ አልጮህኩም፣
የፈለገውን እኩይ ጣጣ
ራስ ላይ የሚወጣ
ቢሆንም እጣ
ይዞ የሚመጣ
ብናድድም ግና አቀርቅሬ
ወይ ተመርሬ ኣላውቅም!
ከዚያ የንዴትና የእንባ
ባድማ ባሻገር
ይታየኛል የመከራ ጥላ
የወረረው መንደር!
አንድ ወቅት ለሌላ
ከነግሳንግሱ
ቢሆንም የሚለቅ ተራ፣
ዘመን ያገኘኛል
ከአይበገሬዎች ጎራ
ሆኜ መጻኢ እጣዬን የማልፈራ!
መሃንዲሰ ነኝ
እጣዬን የምቀይር ቀጥቅጬ፣
የነፍሴን መርከብ
መሪ ጨብጬ!
(ዊሊያም እርነሰት ሔንሊይ) //
Feb 23, 2016
Feb 23, 2016 at 1:35 AM UTC
My love is like to ice, and I to fire
How comes it then that this her cold so great
Is not dissolved through my so hot desire,
But harder grows the more I her entreat?
Or how comes it that my exceeding heat
Is not allayed by her heart-frozen cold,
But that I burn much more in boiling sweat,
And feel my flames augmented manifold?
What miraculous thing may be told,
That fire,which all things melts,
Should harden ice,
And ice,which is congealed with senseless cold,
Should kindle fire by wonderful device?
Such is the power of love in gentle mind,
That it can alter all the courses of kind.
ፍቅሬ እንደ በረዶ ነች
ፍቅሬ እንደ በረዶ ነች እኔደሞ እንደሳት
ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ዝምታዋ የበረታው
በፍላጎቴ ግለት ያልቀለጠው ያልተረታው፣
ይልቅ በቀረብኳት በተማፀንኳት ቁጥር፣
በረዶ፣ በበረዶ ላይ ሚጋግር!
ደሞስ እንዴት ይሆን
የኔ ፍም እሳት
በልቧ ቁር የማይጠፋ የማይዳፈን
ጭራሽ ሙቅ ላቤ የሚንቆረቆር፣
የፍቅሬ ቋያ ሚበረታ እያደር?
ታዲያ ከዚህ የላቀ ምን ታምር ሊነገር፣
ሁሉን አቅላጭ እሳት በረዶ ሲጋግር!
በአንፃሩ ለመኮማተር የማይቸገር
በረዶ ፣ሲሰትዋል ሳተ አንድዶ!
እንግዲህ እንዲህ ነው ጉልበቱ የፍቅር
የነገሮችን ኡደት አፋልሶ የሚቀይር!
(ኤደመንድ ስፔንሰር)//
Jan 27, 2016
Jan 27, 2016 at 8:17 AM UTC
When you lay before me dead
In such pallid rest,
On those passive lips of thine
Not one kiss I pressed!
Did you wonder-looking down
From some higher sphere-
Knowing how we two had loved
Many and many a year?
Did you think me strange and cold
When I didn’t touch
Even with reverent finger-tips
What I had loved so much?
Ah! when last you kissed me,dear,
Know you what you said?
“Take this last kiss my beloved,
Soon shall I be dead!”
“Keep it for a solemn sigh
Through our love’s long night,
Till you give it back again
On some morning bright.”
So I gave you no caress,
But remembering this,
Warm up on my lips
I keep your last living kiss!
የከንፈር ማህተም
ከዚህ ዓለም ተለይተህ
ፀጥ ረጭ ብለህ
ከፊቴ ተዘርግተህ ሳለህ፣
አልሞከርኩም ምንም፣
የማይላወሱ ከንፈሮቸህን ልስም!
ላይ በአፀደነፍስ ሆነህ
ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዓመታት አስበሀ
ይሆን ታዝበህ፣
ወስደህ ይሆን ግምት
ሥታገኝኝ ያለወትሮዬ ጭምት፣
በጣቶቼ ጫፍ ንኳ
የወደድኩትን ማልነካ፣
ግና በመጨረሻ ስትስመኝ
ታስታውስ ይሆን ምን እንዳልከኝ፣
“ውሰጅ ይህን የከንፈር ማሰታወሻ
ተቃርቧል የኔ መጨረሻ!
በፍቅራችን የጨለማ ሠአት
ምልክት ይሁንሽ ምናልባት፣
መልሰሽ አስክትሰጪኝ
አንድ ብሩህ ጠዋት ስታገኚኝ!”
ያልዳበስኩህ ለዚያነው፣
ግን እንዳልከው
ወደኋላ ተመልሼ
መልክቱን አስታውሼ
ያን የመሰነባበቻ የከንፈር ማህተም
ልክ ከንፈሬ ላይ አንዳሳረፍከው
ከነግለቱ ይዤው ነው የምዘልቀው!
(ጁሊያ ካሎሪን) //
Dec 26, 2015
Dec 26, 2015 at 6:01 AM UTC
When Susan’s work was done, she would sit
With one fat guttering candle lit,
And window opened wide to win
The sweet night air to enter in.
There, with a thumb to keep her place
She would read with stern and wrinkled face,
Her mild eyes gliding very slow
Across the letters to and fro,
While wagged the guttering candle flame
In the wind that through the window came
And sometimes in the sentence she
Would mumble a sentence audibly
Or shake her head as if to say,
“ You silly souls, to act this way!”
And never a sound from night I would hear,
Unless some far-off **** crowed clear;
Or her old shuffling should turn
Another page’and rapt and stern,
Though her great glasses bent on me,
She would glance into reality
And shake her round old silvery head,
With-“You!—I thought you were in bed!”
Only to tilt her book again
And rooted in Romance to remain
ባልቴቷ ሱሳን
ሱሳን ሥራዋን ሰራርታ
ትቀመጣለች ወፈር ያለ
ሻማ አብርታ፣
መስኮቷን አርጋ
በሰፊው ከፈት
ባለግሩም መአዛውን
የማታ አየር
በደንብ ለመሸመት!
ገፁ እንዳይጠፋባት
አልባ በአውራ ጣት፣
ሻማዋን ንፋሱ እያንገላታት
ተመስጦ በሚስተዋልበት
ቅጭም ያለ ፊት
እየተደመመች ታነባለች
ዓይኗን ከዚህ ወደዚያ
ወደዚህ ከዚያ
በፊዴሎቹ ላይ
እያደረገች ሸርተት፡፡
በዛ ኮሽታ አልባ ፀጥታ
ይሰማል በለሆሳስ ስትናገር
የሆነ ነገር
ወይ ጭንቅላቷን ነቅንቃ ስታበቃ
ስትል ‹‹ምን አይነት ናችሁ
እንዴት ንደዚህ ታደርጋላቸሁ?››
ከሩቅ አውራ ዶሮ ኩኩሉ
ረጭ ብሏል ሥፍራው ሁሉ--
አይሰማም ምንም ድምፅ
ካልሆነ መፅሐፍ ሲገለፅ፡፡
በትልቁ መነፅሯ ልታይ ዙራ፣
ሥፍራውን ማትራ፣
ሽበት ቀመስ ጭንቅላቷን
እየነቀነቀች ወደኔ ያየች
‹‹አንተ ገና አልተኛህም?››
ትለኛለች
ዳግም ወደመፅሓፏ ተመልሳ፣
በተመስጦ የፍቅር ታሪከ ውስጥ
ራሷን ልትረሳ!
(በዋልተር ዲላሜር)//
Dec 28, 2015
Dec 28, 2015 at 1:35 AM UTC
What worlds of wonders are our books
As one opens them and looks,
new ideas and people rise
In our fancies and our eyes
The room we sit in melts away,
And we find ourselves at play
With someone who before the end,
May become our chosen friend
We sail along the page
To some other land or age.
Here is our body in the chair
But our mind is over there.
Each book is a magic box
Which with a touch
A child unlocks.
In between their outside cover
Books held all things, for their lover
መፃሕፍት
ገልፆ ለሚያያቸው
መሕፍት ምንኛ
ድንቅ ዓለሞች ናቸው፣
በምናባችን በዓይኖቻችን ማእዘን
ይከስታሉ አዳዲስ ሓሳቦች፣
እንዲሁም ልዩ ልዩ ሰዎች!
የተቀመጥንበት ክፍል ድንገት
ጅረት ይሆንና
ይዞን ሲነጉድ
እስከጥግ ሳንዘልቅ ገና
እንተዋወቃለን ሠዎች ደና
የሚያደርጉን ዘና፣
ምናልባትም ለዘልቄታው
የሚሆኑን የኛ
ምርጥ ጓደኛ!
አሊያም ገጾቹን ቀዝፈን
ራሳቸንን ናገኛለን
ወደሌላ ያለም ማዘን
ወይ ዘመን ተጓጉዘን
‘ዚህ ወንበር ላይ
በአካል ተቀምጠን
በምናብ ተሻግረን ዛነን፡፡
‘ያንዳንዱ መፅፍ
የድንቃድንቅ ማህደር ነው
‘ያንዳንዱ ህፃን ይዞ
ሚከፍተው ቁልፉን ጠምዞ፡፡
አጥብቆ ለሚሻቸው
በውጪ ልባሶቻቸው
መፃሕፍት ሸክፈዋል
ሁሉን አቅፈው!
(ኢሌኖር ፍራጂዮን) //
Jan 21, 2016
Jan 21, 2016 at 4:19 AM UTC
My heart is heavy with many a song
Like a ripe fruit bearing down the tree,
But I can never give you one—
My songs don’t belong to me.
Yet in the evening,in the dusk
When moths go to and fro
In the Gray hour
If the fruit has fallen,
Take it no one will know.
ልቤ ከብዷል
እንዳጎነበሰ ዛፍ የበሰለ ፍሬ አግቶ
ልቤ ከብዷል በመዝሙር ተሞልቶ፣
ግን አንድ በፍጹም ልሠጥህ አልችልም፣
መዝሙሮቼ የኔ አይደሉም!
ሆኖም በጠፍ ጨረቃ ማታ
ነፍሳት ሲወራጩ ከቦታ ቦታ
በግራጫማዋ ሠአት
ፍሬ ከወደቀ ምናልባት
ውሰድ- ማንም አያውቅም!
(ሳራ ቲሰዳል) //
Jan 5, 2016
Jan 5, 2016 at 1:59 AM UTC
There is a lady sweet and kind
was never face so pleased my mind,
I did but see her passing by
And yet I love her till I die.
Her gesture,motion,and her smiles,
Her wit,her voice my heart beguiles,
Beguiles my heart,I know not why
And yet I love her till I die.
Cupid is winged and doth range,
Her country so my love doth change
But change she earth or change she sky,
Yet will I love her till I die!
(Anonymous)
አለች ጥሩ እመቤት የምትናፈቅ ሴት
ማራኪ ጥሩመቤት
አለች አንድ የምትናፈቅ ሴት!
አስደሳች ፊቷ
ይሰጠኛል የውስጥ እርካታ!
ሥታልፍ በደንብ አይቼአታለሁ
ግና እስትሞተ አፈቅራታለሁ!
በእንቅስቃሴዋ
በግሩም ፈገግታዋ
በድምጿ
ልቤ ይርዳል፣
ልቤ ለምን አንደሚርድ
ባላወቅም
‘ሷን ማፍቀር አላቆምም!
‘ንደሚታወቅው ኩፒድ
(የፍቅር መላክ )
ክንፍ ስላለው
የሚጓዝ ነው፣
ፍቅሬ ወደ መሬት
ወይ ወደ ሰማይ ብትቀየር
አላቆምም ‘ሷን ማፍቀር!
(ያልታወቀ ደራሲ)
Feb 13, 2016
Feb 13, 2016 at 7:22 AM UTC
I will be the gladdest thing
under the sun!
I will touch hundred flowers
And not pick one.
I will look at cliffs and clouds
With quiet eyes
Watch the wind bow down the grass,
And the grass rise.
And when lights begin to show
Up from town
I will mark which must be mine
And then start down!
ተራራው ጫፍ ከቀትር በኋላ
ከፀሐይዋ ሥር
እሆናለሁ
ደስተኛ ፍጡር
አቻአልባ በንፅፅር!
መቶ አበባዎች ብዳብስም
አንዲት እንኳን አልቀጥፍም!
እንደዚሁም በመደመም
እመለከታለሁ
ኮርብታውን ተራራውን
ሲያስጎነብሰው ንፋሱ ሳሩን
ሲነሳ ሳሩ ተራውን!
ከተማዋ ከሩቅ
በመብራት ስታሸበርቅ
ብዙም ሳልጠብቅ
ጠንቅቄ የኔን መንደር
እጀምራለሁ ቁልቁል መንደርደር::
(ኤድና ሴንት ቪኒሰንት ሚሌ) //
Jan 6, 2016
Jan 6, 2016 at 2:35 AM UTC
Fathers are wonderful people
Too little understood,
And we do not sing their praises
As often as we should...
For, somehow, Father seems to be
The man who pays the bills,
While Mother binds up little hurts
And nurses all our ills...
And Father struggles daily
To live up to 'his image'
As protector and provider
And 'hero of the scrimmage'...
And perhaps that is the reason
We sometimes get the notion,
That Fathers are not subject
To the thing we call emotion,
But if you look inside Dad's heart,
Where no one else can see
You'll find he's sentimental
And as 'soft' as he can be...
But he's so busy every day
In the gruelling race of life,
He leaves the sentimental stuff
To his partner and his wife...
But Fathers are just wonderful
In a million different ways,
And they merit loving compliments
And accolades of praise,
For the only reason Dad aspires
To fortune and success
Is to make the family proud of him
And to bring them happiness...
And like Our Heavenly Father,
He's a guardian and a guide,
Someone that we can count on
To be always on our side.
(Helen Steiner Rice)
አባቶች ግሩም ሰዎች ናቸው
አባቶች ግሩም ሰዎች ናቸው ፣
ምንም እንኳ ባይታደሉም በደንብ የሚረዳቸው
የሚገባቸውን ምስጋና፣
በስፋት አልዘመርንም ገና!
ምክንያቱም አባታችን
የወጪያችን ሽፋን ሆኖ
ስለሚሳል በእይታችን፣
በአንፃሩ እናታችን
ሐኪም የቁስላችን
ለሷ ህመማችን ነው የጋራችን፡፡
ቆፍጣና፣ የተንከባካቢነት፣ የአስተዳዳሪነት
ብሎም የችግር ፍቺነት ተግባር
ለማስጠበቅ የሚጥር ዘወትር
ለዚህ ይሆን ምናልባት
አባቶች ተገዢ የማይመስሉን ለስሜት?
ግን የአባባን ልብ ብታዩት
ባትታደሉም ያን ለማየት
ታስተውሉ ነበር በውነት
ያቺን ቡብነት የሚያምሳትን
የልቡን ስሱነት!
በሥራ ከመጠመድ ነው
በዚህ አታካቹ ሩጫ የህይወት
ጉዳዮችን የስሜታዊነት
ለውሀ አጣጩ ለሚስቱ የሚተውላት!
ግን አባቶች በጣም ግሩሞች ናቸው
በሚሊዮን መንገድ
የፍቅር ምላሽ ምስጋና የሚገባቸው
ብቸኛው ምክንያት፣ አባባ ሁሌ የሚሯሯጠው
ቤተሰቡን ለማስደሰት ለማኩራት ነው
ልክ እንደሰማዩ አባታችንሁሌ ያለ ከጎናችን
ነው መከታችን
በሄለን ስቲነር ትርጉም ዓለም ኃይሉ
Jun 22, 2020
Jun 22, 2020 at 2:02 AM UTC
I see their faces
Children I played with when I was a child
Loise comes back with her brown hair braided
Annie with ringlets warm and wild
Only in sleep time is forgotten—
What may have come to them , who can know?
Yet we played last night as long ago,
And the doll-house stood at the turn of the stair
The years had not sharpened their smooth
Round face,
I met their eyes and found them mild-
Do they too, dream of me, I wonder
And for them am I too a child?
በህልም ብቻ
በእንቅልፌ ፊታቸው ውል ይለኛል ድንገት፣
አፈር ፈጭተን ያደግን በልጅነት፣
ሊዊሰ ትመጣለች ቀይ ፀጉሯ አንደተጎነጎነ
አኒ አንደተቆጣጠረ እንደተበታተነ፣
በእንቅልፍ ብቻ
ጊዜው ነጉዷል
ግን ምን አዳጋጠማቸው ማን ያውቃል?
ሆኖም ትናንት አንደጥንቱ
አብረን ተጫውተናል!
አጠፍ ብሎ ከደረጃው መወጣጫ
ይስተዋላል ያ ክፍል
የአሻንጉሊቶቹ ማስቀመጫ፡፡
የነጎዱት ዓመታት፣
ክብና ጥርት
ያሉ ፊቶቻቸው ላይ አላሳረፉም ጭረት፣
የመጨራመት ምልክት!
ዓይን ለዓይን ስንተያይ
ይልቅ ደህና ነገር ነው የማይ፣
‘ነሱም ስለኔ ያስቡ ይሆን?
ይለኛል ድንቅ
ደሞስ እኔ እንዳገኘኋቸው
ልጅ ሆኜ ይሆን የምታያቸው?
(ሳራ ቲሰዳል ) //
Jan 16, 2016
Jan 16, 2016 at 3:26 AM UTC
The rose in the garden slipped her bud
And she laughed in the pride
Of her youthful blood
As she thought of the Gardner standing by—
‘’He is old—so old! And he soon must die!’’
The full Rose waxed in the warm June air
And she spread and spread till her heart lay bare;
And she laughed once more as she heard his tread—
“He is older now! He will soon be dead!’’
But the breeze of the morning blew, and found
That the leaves of the blown rose strew the ground
And he came at noon, that gardener old,
And he raked them gently with the mould.
And I wove the thing to a random rhyme,
For the rose is beauty, the gardener, time.
ቀበጧ ፅጌረዳ
እንቡጥ ፅጌረዳ አንገቷን ሰገግ አርጋ
ብቅ አለች ከአትክልቱ ሥፍራ በአበቦቹ አልጋ
አፍላ የወታጣትነትን ወራት
የሚያጅበው የትኩስ ደም ኩራት
በቃ አፍነከነካት!
ከጎኗ አትክልተኛውን ቆሞ ስታስተውል
የሓሳብ ብርቅታ አላት ውል
‹አርጅቷል በጣም አርጅቷል
በቅርቡ ይሞታል!›
ሞቃታማው የበጋ አየር ስለተስማማት
ክንፎቿን ዘርግታ በስፋት
ምንም ለመደበቅ ሳትዳዳ
ከፈተች የልቧን ጓዳ::
ስትሰማ የእግሩን ኮቴ አንደገና
አሳቃት ደና... ‹አርጅቷል፣ አፍጅቷል
ብዙ ሰንብቷል፣
አሁንስ ይሞታል!›
ግና የማለዳው ንፋስ ደርሶ
ስፍራውን አተራምሶ
ሲሄድ ተጣድፎ
አስተዋለ የፅጌረዳ ክንፍ
በአትክልቱ ቦታ ተነስንሶ፣
ቀተር ላይ አዛውንቱ አትክልተኛው
ሑሉንም በሹካው ሰብስቦ ከላው!
እናም በዚህ ጉዳይ ስለተመሠጥኩ
የስንኝ ቋጠሮ ከተብኩ
እኔ እንዳስተዋልኩት
ፅጌረዳዋ የውበትን
አትክልተኛው የጌዜን
ምስል ነው የሚከስቱት!
(አውሰቲን ዶብሶን) //
Jan 4, 2016
Jan 4, 2016 at 9:24 AM UTC
Sir,I admit your general rule,
That every poet is a fool,
But you yourself may serve to show it
That every fool is not a poet.
እምቅ ድድር
(ገጣሚ ሞኝ ነው)
ጌታው በደምሳሳው
‹‹ገጣሚ ሞኝ ነው!››
የምትለውን ቢሆንም
የምቀበለው፣
ሞኝ ሁሉ ግን ገጣሚ
እንዳልሆነ ለማሳየት
ከአንተ ሌላ ምሳሌ
አያሻም ምናልባት!
(ሳሙኤል ኮልሪዲጅ)//
Mar 4, 2016
Mar 4, 2016 at 1:15 AM UTC