Submit your work, meet writers and drop the ads. Become a member
Dec 2015
የሆነ ቀን ነው ነገሩ የተከሰተው፣
ዓመቱ ተገባዶ ሲሰናበት፣
ደርቦ ካባ ፀዓዳ ወተት!
ሊጎበኙት መጡ ሁለት ጎረቤቶች፣
የኮናርድ አብሮአደጎች፣
ወና ሆኖ ተዳክሞ አገኙት ሱቁን፣
ገርጥቶ ተቆራምዶ እሱን!
ተወት አድርጎ የሚሰፋውን፣
ፈልጎ እንዲሰሙ የሚለውን፣
“ባንጀሮቼ አድምጡኝ፣
ዛሬ በማለዳ
አውራ ዶሮ ሌሊቱን
በጩከት ሲሸኝ፣
ጌታ በሕልሜ ተገልፆ
ይህን አለኝ
‘እመጣለሁ ቤትህ፣ ልጎበኝህ!’
ይኸው አለሁ
ያለፋታ ቤቴ ውስጥ እንዲሁ ስመላለስ፣
የፅድ ዝንጣፊ ስቆርጥ ስነሰንስ፣
ጠረጴዛውን ስዘረጋ - ስጎትት ሳስጠጋ፣
የሻይ ጀበናውን ስፍቅ - እስኪያብረቀርቅ!
በመለጠቅ አድርጊያለሁ ደማቅ፣
ባለቀይ ኳስ ገመድ፣
በሸሪራዎቹ ቁልቁል ተንጠላጥሎ፣
በየአቅጣጫው እንዲወርድ!
እናም እስኪገለጥልኝ ጌታ፣
እየተጠባበቅኩ ነው የእግሩን ኮሽታ፣
ሲገለጽ በሬን ከፍቼ፣
ፊቱን ለማየት ጓጉቼ፣
ትንሽ ተጠግቼ!”
ባልንጀሮቹ የሚለውን ሰምተውት፣
ሄዱ ቤታቸው ብቻውን ትተውት!
እሱ እንደው፣
በጣም የተደሰተበት ወቅት ነው፡፡
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቹ
ተራ በተራ ሞተዋል፣
ኮናርድም ብዙ ብቸኛ ቀዝቃዛ
ገናዎች አሳልፏል!
ሆኖም ነበረው ትልቅ እምነት፣
በእንግድነት ስለሚገኝለት፣
ጌታ ያቺን ቀን፣ ቤቱን እንደሚያደምቅለት!
ነበር ተደስቶ፣
የሚያደምጥ ጆሮውን አንቅቶ!
ድምፅ ሰምቶ ቀጥ አለ በቅፅበት፣
መጥቶ እንደው ጌታ ድንገት፣
ለብርቱ ፀሎቱ ምላሽ ለመስጠት!
ወደ መስኮቱ ሮጦ ሲጠጋ
በዚያ በረዶ የሸፈነው፣
አስፋልት ላይ ያየው፣
ብትቶ የለበሰ ለማኝን ነው -
ምስኪን፣ አፍንጫው የተገነጠለ፣
ጫማ፣ የተጫማ!
“ደንዝዞ ቆስሎ ይሆናል እግርህ፣
ጫማ አለ ሱቄ በልክህ፣
ግባ ልስጥህ-
ኮትም የሚያሞቅህ!”
ለማኙ የሚፈልገውን አግኝቶ፣
ወጥቶ ሄደ ረክቶ!
ኮናርድ ግን
በመገረም ጌታ ለምን እንደቆየ፣
ሰዓቱን አየ፡፡
ከዚያም ቆመ ግራ በመጋባት፣
መቆየት እንዳለበት፣
ምን ያህል ተጨማሪ ሰዓት?
ግን ድንገት፣
ኳኳ የሚል ድምጽ ሰምቶ፣
በሩን ከፈተ ወደዚያ አምርቶ፡፡
ግን እንደገና አየ ሌላ እንግዳ፣
የፈለገች ለመዝለቅ ከጓዳ፣
አረጋዊት የጎበጠች፣
ቲውቢት የደረበች፣
ትንሽ ጭራሮ ከጀርባዋ የሸከፈች፣
እናም እረፍት የማድረጊያ ቦታ ጠየቀች፡፡
ለታላቁ እንግዳ በቀር፣
ሌላ ስፍራ አልነበር!
ጥያቄዋ የመማፀን ድምፀት፣
ነበር የተጫነበት፣
ኮናርድ ‘ቤት ለእንግዳ’ ብሏት፣
ሻይ አፍልቶላት
ከጠረጴዛው እንድታርፍ ጋብዟት፣
እነሆ ጠጪ አላት፡፡
ግን እሷን እንደሸኘ አዘነ፣
ሰዓቱ እያለፈ ስለሆነ!
ደሞም ጌታን ሲጠብቀው ስለቀረ፣
መልክቱን በደንብ ማድመጡን ተጠራጠረ!
ሀዘን ገብቶት ሲያቅማማ፣
ሌላ ድምፅ ሰማ!
“እባክህ እርዳኝ
የት ነው ያለሁት?”
ዳግም የደግነት በሩን ሲከፍት፣
ለሶስተኛ ጊዜ አለው ክፍት!
መንገድ የጠፋት ልጅ ነበረች፣
ሳታስበው በገና ቀን
ከቤተሰቧ ተለይታ የሄደች!
የኮናርድ ልብን ሀዘን ገባው፣
ቢሆንም ልጅቷን ማፅናናት እንዳለበት ተሰማው!
“ግቢ ልጄ” ብሏት እንባዋን አበሰላት፣
እንዳትረበሽ አረጋጋት፣
ቤቷም ድረስ ሸኛት!
ተመልሶ ሲገባ፣
ወደ ክፍሉ ሞገስ አልባ
“በቃ አለቀ ደቀቀ
ቀኑም ተጠናቀቀ!” ብሎ ተሳቀቀ፡፡
ያም ሆኖ
ስሜቱ እንደቀዘቀዘ፣
መፀለይ ያዘ!
“ጌታ ለምን ዘገየህ፣
ቤቴ እንዳትመጣ ምን ያዘህ?”
እያለ ቅሬታ ሲያሰማ
እንግዳ ድምፅ ሰማ
‘ጭንቅላትህን ወደ ላይ አንሳ፣
እኔ እንደው ቃሌን አረሳ!
በደጅህ በምድራኳ፣
በጥላዬ ተጠግቼ በርህን ላንኳኳ፣
ሶስቴ ጎብኝቼሀለሁ ዛሬእንኳ!
እኔ ለማኙ ነበርኩ፣
የቀረብኩህ ብትቶ እንደደረብኩ!
ደሞም ከድካሟ የታደግካት፣ ባልቴት፣
በመጠለያ አልባው ውርጫማው መንገድ፣
ለሆንካትም ልጅ ዘመድ’
(በሔለን ስቲነር ራይስ )
I think this  is the best poem about Christmas,we have to support the needy. I translated it in Amharic. Google and read Helen Stiner Rice's poem 'Christmas Guest'
The Americans call her an Ambassador of Sunshine for her uplifting poem
© Alem Hailu Gabre Kristos
Written by
Alem Hailu GKristos  Ethiopia
(Ethiopia)   
  1.2k
   Samuel Hesed
Please log in to view and add comments on poems