She stood breast high amid the corn
Clasp’d by the golden light of morn,
Like the sweetheart of the sun,
Who many a glowing kiss had won.
On her cheek an autumn flush,
Deeply ripen’d;—such a blush
In the midst of brown was born,
Like red poppies grown with corn.
Round her eyes her tresses fell,
Which were blackest none could tell,
But long lashes veil’d a light,
That had else been all too bright.
And her hat, with shady brim,
Made her tressy forehead dim;—
Thus she stood amid the stooks,
Praising God with sweetest looks:—
Sure, I said, Heav’n did not mean,
Where I reap thou shouldst but glean,
Lay thy sheaf adown and come,
Share my harvest and my home.
ሩት
እስከ ጡቷ ከፍታ
የተንጣለለ የበቆሎ ማሳ ውስጥ ገብታ፣
የማለዳው ወርቃማ ጮራ
በዙሪያዋ ዘሃውን እያደራ፣
ሠምጣ ቆመች፣ በእጹብ ድንቅ ግርማ
እንደፀሐዩ ፍቅረኛ ደጋግማ
በጨረር ተስማ ተሸላልማ፡፡
ልክ ከበቆሎ የማሳ ዳራ
ብቅእዳለቸ ዓይን የምታስር አበባ
የተገኘች ከጠይሞች ጎራ፣
እንደበሠለ ፍሬ እንደጎምራ
ጉንጮችዋ ቀልተዋል አፍራ!
ብርቅዬ ጥቁር ሐር
የፀጉሯ ዛላ ተዘናፍሎ
ይስተዋላል ቅንጦቿዋን
ደገፍ ደገፍ ብሎ፣
ግና የዓይኖቿ ሽፋሽፍት
ብርሃን እምቅ አድርገዋል ድብቅ
አሊያ በጣም የሚያንፀባርቅ!
የኮፍያዋ ጥላ ፊቷን አጠይሞት
ከበቆሎው ምርት ቆማለች
ሐአሴት እያደረገች፣
አምላኳን እያመሰገነች!
በርግጥም አልኩ
አምላክ አላሰበም
እኔ ሳጭድ እሷ እንድትሸከም፡፡
በክርንሽ የሸከፍሽውን ለቀሽ
ወደኔ ነይ፣
ምርቴና ቤቴን ተካፈይ!
(ቶማሰ ሁድ) //
Yes original,natural or organic beauty is superb