Submit your work, meet writers and drop the ads. Become a member
Apr 2016
(Storms Bring Out the Eagles But The Little Birds
Take Cover )
When the “storms of life” gather darkly ahead,
I think of these wonderful words I once read
And I say to myself as “threatening clouds” hover
Don’t “fold up your wings” and “run for cover”
But like the eagle “spread wide your wings”
and “soar far above” the trouble life brings,
For the eagle knows that the higher he flies
The more tranquil and brighter become the skies...
And there is nothing in life God ever asks us to
bear
That we can’t soar above “On The Wings Of A
Prayer,”
And in looking back over the “storm you passed
through”
You’ll find you gained strength and new courage,
too,
For in facing “life’s storms” with an eagles wings
You can fly far above earth’s small, petty things.

ወጀብ ንስሮችን ያወጣል

(ግና ትናንሽ ወፎች ከመጠለያ ይመሰጋሉ)

የሕይወት ወጀብ ሲሰባሰብ፣
ደሞም ከስሎ ከላዬ ሲሳብ፣
እገባለሁ ማሰብ፣
ግሩም ምክሮችን እነኚህን፣
በአንድ ወቅት የሰማሁትን!
‘ለራሴ እንደዚህ እላለሁ
አስፈሪ ደመናዎች ሲያንዣብቡ፣
ክንፋችሁን አታስገቡ፣
ደሞም ሮጣችሁ
ሆናችሁ ጉጉ፣
ከመጠለያ አትመሰጉ!
ግን እንደንስር ክንፋችሁን ዘርጉ፣
ሕይወት ከሸከፈው ችግር በእቅፉ፣
ሽቅብ ሰንጥቃችሁ ተንሳፈፉ!
ምክንያቱ ያውቃል ንስር፣
ሽቅብ ሰንጥቆ ሲበር፣
ሰማዩ እንደሚቀየር፣
ወደብሩህ ጠፈር፣
ሰላምና መረጋጋት፣
ያደረጉት ግዛት!’
ሕይወትን ካጤንነው፣
እንድንቋቋመው የተጠበቅነው፣
ነገር ወይ ክስተት፣ ዘበት፣
በፀሎት ክንፍ፣ የማንለው እልፍ!
ያን በወጀብ የተናጥንበት
የትናንት ሕይወት፣
በምልሰት ስንመለከት፣
እናስተውላለን
አዲስ ተስፋና ብርታት፣
እንደሚሆኑን ተደራቢ ሀብት!
ሽቅብ በንስር ክንፍ፣
የሕይወትን አውሎንፋስ
ጥሳችሁ ስትሉ እልፍ፣
የመሬትን ጥቃቅን አለመመቻቸቶች
ረግጣችሁ፣ ትንሳፈፋላችሁ!

(በሔለን ስቲነር ራይስ)
Uplifting poems
Written by
Alem Hailu GKristos  Ethiopia
(Ethiopia)   
2.1k
 
Please log in to view and add comments on poems