Submit your work, meet writers and drop the ads. Become a member
Jan 2016
The rose in the garden slipped her bud
And she laughed in the pride
Of her youthful blood
As she thought of the Gardner standing by—
‘’He is old—so old! And he soon must die!’’
The full Rose waxed in the warm June air
And she spread and spread till her heart lay bare;
And she laughed once more as she heard his tread—
“He is older now! He will soon be dead!’’
But the breeze of the morning blew, and found
That the leaves of the blown rose strew the ground
And he came at noon, that gardener old,
And he raked them gently with the mould.
And I wove the thing to a random rhyme,
For the rose is beauty, the gardener, time.

ቀበጧ ፅጌረዳ

እንቡጥ ፅጌረዳ አንገቷን ሰገግ አርጋ
ብቅ አለች ከአትክልቱ ሥፍራ በአበቦቹ አልጋ
አፍላ የወታጣትነትን ወራት
የሚያጅበው የትኩስ ደም ኩራት
በቃ አፍነከነካት!
ከጎኗ አትክልተኛውን ቆሞ ስታስተውል
የሓሳብ ብርቅታ አላት ውል
‹አርጅቷል በጣም አርጅቷል
በቅርቡ ይሞታል!›
ሞቃታማው የበጋ አየር ስለተስማማት
ክንፎቿን ዘርግታ በስፋት
ምንም ለመደበቅ ሳትዳዳ
ከፈተች የልቧን ጓዳ::
ስትሰማ የእግሩን ኮቴ አንደገና
አሳቃት ደና... ‹አርጅቷል፣ አፍጅቷል
ብዙ ሰንብቷል፣
አሁንስ ይሞታል!›
ግና የማለዳው ንፋስ ደርሶ
ስፍራውን አተራምሶ
ሲሄድ ተጣድፎ
አስተዋለ የፅጌረዳ ክንፍ
በአትክልቱ ቦታ ተነስንሶ፣
ቀተር ላይ አዛውንቱ አትክልተኛው
ሑሉንም በሹካው ሰብስቦ ከላው!
እናም በዚህ ጉዳይ ስለተመሠጥኩ
የስንኝ ቋጠሮ ከተብኩ
እኔ እንዳስተዋልኩት
ፅጌረዳዋ የውበትን
አትክልተኛው የጌዜን
ምስል ነው የሚከስቱት!
(አውሰቲን ዶብሶን) //
Who are we to interfere in the works of God?
Written by
Alem Hailu GKristos  Ethiopia
(Ethiopia)   
793
 
Please log in to view and add comments on poems